ለቅድመ መደበኛ እና 1ኛ ደረጃ መምህራን በአዲሱ የትምህርትና ስልጠና አቅጣጫ መሰረት ስልጠና እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
አዲሱን የትምህርትና ስልጠና አቅጣጫ መሰረት በማድረግ ለቅድመ መደበኛ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መምህራን በሚሰጠው ስልጠና ላይ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።
የትምህርት ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ ገረመው ሁሉቃ (ዶ/ር) የትምህርትን ጥራት ለማረጋገጥ መምህራን የአዲሱን የትምህርትና ስልጠና አቅጣጫን መሰረት ያደረገ ስልጠና መውሰድ እንደሚገባቸው በውይይቱ ገልፀዋል፡፡
ክልሎች ላይ የሚገኙ የመምህራን ትምህርት ኮሌጆች ውስጥ የሚሰጡ የመምህራን ስልጠናዎች አዲሱን የትምህርትና ስልጠና መርሀ-ግብር መሰረት ሊያደርጉ እንደሚገባቸው ተነግሯል፡፡
በመድረኩ ላይ የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች፣ የ39 የመምህራን ትምህርት ኮሌጆች ዲኖች እና የትምህርት ሚኒስቴር ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
#news