በቅርቡ በትምህርት ሚኒስቴር ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ እንዲደረግ የተወሰነው ሥርዓተ ትምህርት
በቅርቡ በትምህርት ሚኒስቴር ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ እንዲደረግ የተወሰነው ሥርዓተ ትምህርት አብዛኛውን የማኅበረሰብ ክፍል እና ምሁራንን ሲያነጋገር እንደነበር ይታወሳል፡፡
ሥርዓተ ትምህርቱ ‹‹የግል ትምህርት ቤቶችን ያላማከለና በቂ የሆነ ጥናት ያልተደረገበት›› በማለት የሚከራከሩም አሉ፡፡
ሥርዓተ ትምህርቱ ከመስከረም 2015 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ መደረግ ቢጀምርም የውጭ አገር ሥርዓተ ትምህርትን የሚከተሉ የግል ትምህርት ቤቶች አሉ፡፡
መንግሥት ሥርዓተ ትምህርቱ በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች እንዲተገበር በጥብቅ ያሳሰበና ይህንን በማይተገብሩ ላይ ዕርምጃ እንደሚወስድ ያስታወቀ ቢሆንም እምቢተኝነቱ ይታያል፡፡
የትምህርትና ሥልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለሥልጣን ከአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ፣ ከመንግሥትና ከግል ትምህርት ቤቶች ከተውጣጡ ኃላፊዎች ጋር በአፍ መፍቻ ቋንቋ እና በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ትግበራ ዙሪያ ውይይት መደረጉን ሪፖርተር ዘግቧል፡፡
@TIMIHIRT_MINISTER
@TIMIHIRT_MINISTER