Latest Blog

Get latest news about education and academics | በየለቱ የሚቀርቡ ትኩስ ትምህርታዊ ዜናዎችን ያግኙ

በመጪው ሰኞ የትምህርቱን ዘመን አጀማመር ምልከታ ይደረጋል

 መጪው ሰኞ ጀምሮ በሁሉም ክልሎች የ2012 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን አጀማመር ምልከታ እንደሚደረግ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

******************************************************************************

በትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ቤት መሻሻልና ፕሮግራሞች ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ አማካሪ አቶ ዳዊት አዘነ ዛሬ እንዳስታወቁት ከሰኞ መስከረም 12 እስከ ዓርብ መስከረም 16 ድረስ የትምህርት ሳምንት አጀማመር ምልከታ በሁሉም ክልሎችና በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች ይከናወናል፡፡

በምልከታው በሁሉም ከተሞችና የከተማ አስተዳደሮች ውስጥ የሚገኙ 36 ዞኖችና 144 ትምህርት ቤቶች የመጀመሪያው ትምህርት ቀንና የትምህርት ሳምንት አጀማመር እና አፈጻጸም ግምገማ እንደሚደረግ አቶ ዳዊት ተናግረዋል፡፡

በአስራ ሁለት ቡድኖች ተከፍሎ ስምሪት የሚያደርገው የኢንስፔክሽን ቡድን ከመስከረም 12 እስከ 16 በሚያደርገው ምልከታ 72 የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶችና 72 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተገኝቶ ምልከታ እንደሚያደርግ የሚኒስትር ደኤታ አማካሪው መግለጻቸውን የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዘግቧል፡፡

REGISTER NOW

የ ሒሳብ ችሎታዎን ያዳብሩ

Search