በአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር ጌታቸው ቢያዝን ለክልሉ ቴሌቪዥን (አማራ ቲቪ) ከተናገሩት የተወሰደ፦
- የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሀገር ዓቀፍ ፈተና በተሟላ መልኩ አስፈላጊውን ቅጽ (ፎርም) አልሞሉም ሆኖም የግል ተፈታኞችን ጨምሮ ከ90 ሺህ በላይ ፈተናውን ይወስዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።
- ትምህርት ቤቶች በተለይ 8ኛ እና 12ኛ ክፍሎች ላይ ትኩረት ሰጥተው እንዲሠሩ ለማድረግ ጥረት ተደርጓል።
- አብዛኛው በሚባል መልኩ የአማራ ክልል ተማሪ ገጠር አካባቢ እንደመኖሩ በሚፈለገው ልክ ጥረቱ ውጤት አስመዝግቧል ማለት አይቻልም።
- ተማሪዎች የመማሪያ መጻሕፍቶቻቸው በእጃቸው ስላሉ እንዲያነብቡ፣ የ11ኛ ክፍል ትምህርቶችን መልሰው እንዲከልሱና ወላጆች ለልጆቻቸው አጋዥ መጻሕፍትን እንዲገዙላቸው መልእክት ተላልፏል።
- ሀገር አቀፍ ፈተናው በኢንተርኔት በመታገዝ በቀጥታ (ኦንላይን) እንደሆነ ከዚህ ቀደም ተገልጿል ፤ ተማሪዎች “ታብሌት” ተሰጥቷቸው እንዴት ጥያቄዎችን መሥራት እንዳለባቸው ከቴክኖሎጂ ውጤቱ ጋር የመለማመጃ ጊዜ ይኖራቸዋል።
- ሀገር አቀፍ ፈተናው መቼ እንደሚሰጥ በትምህርት ሚኒስቴርም ይሁን በሀገር ዓቀፍ የፈተናዎች ኤጀንሲ ይፋ አልተደረገም።
- ትምህርት ከተጀመረ የመጀመሪያዎቹ 45 ቀናት ለ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ተፈታኝ ተማሪዎች የክለሳ ጊዜያቸው ይሆናል።