ትምህርት ሲጀመር የትምህርት አሳጣጥ ሂደቱ በፈረቃ እንደሚሆን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።
በፈረቃ የሚሰጠው ትምህርት እንደየአካባቢው ሁኔታ ከ2 እስከ 3 ፈረቃ ተከፍሎ ሊሰጥ እንደሚችልም ተገልጿል።
የመማር ማስተማር ሥራው በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች እንደሚጀመር ትምህርት ሚኒስቴር አመልክቷል።
ሚኒስቴሩ እንዳለው በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ለሰባት ወራት ተቋርጦ የቆየው መደበኛ ትምህርት አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ዳግም ለማስጀመር አስፈላጊው ዝግጅት ተጠናቋል።
መንግስት በትምህርት ቤቶች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ፣ ውሃ እና የእጅ ማጽጃዎችን በማሟላት እንዲሁም ትምህርት ቤቶችን በማጽዳት መደበኛው ትምህርት እንደሚጀመር አስታውቋል - (ኢዜአ)