የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ሐረጓ ማሞ ከ12ኛ እና ከ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ጋር በተያያዘ ተከታዩን ብለውናል ፦
የ12ኛ እና የ8ኛ ክፍል ፈተና በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዲሰጥ በቅድሚያ ትምህርት ቤቶች ኮቪድ-19 መከላከልን መርህ ባደረገ መልኩ ዝግጅት ሙሉ በሙሉ ማጠናቀቅ ይጠበቅባቸዋል።
- ከፈተናው አስቀድሞ የትምህርት ቤቶችን ዝግጁነት የማረጋገጥ ስራ በትምህርት ሚኒስቴር ይሰራል።
- ይህ ተግባራዊ እንዲሆን ሁሉም ትምህርት ቤቶች ፣ የጤና ተቋማት፣ ወላጆች፣ አጠቃላይ ማህበረሰቡ ርብርብ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።
- የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች የ11ኛ ክፍል ትምህርት ያጠናቀቀቁ እና የ12ኛ ክፍልን የመጀመሪያ ሴሚስተር ትምህርት የተከታተሉ መሆን አለባቸው።
- የ8ኛ ክፍል ተፈታኛ ተማሪዎች የ7ኛ ክፍል ትምህርት ያጠናቀቁ እና የ8ኛ ክፍልን የአንደኛ ሴሚስተር ትምህርት የተከታተሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
- ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው በሙሉ አቅም እንዲመለሱ የስነ ልቦና ድጋፍ ይደረግላቸዋል።
- የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና እና ምዝገባ በኦንላይን ይካሄዳል። ተማሪዎች የ45 ቀን የክለሳ እና የቴክኖሎጂ መለማመጃ ጊዜም ይኖራቸዋል።
- በነገራችን ላይ ትምህርት ቤቶች የሚከፈቱት ፣ ፈተናዎችም የሚሰጡት ትምህርት ቤቶች አስፈላጊውን ቅድመ ጥንቃቄ ማሟላት ሲችሉ #ብቻ ነው።
- ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት ቤቶች እንዲከፈቱ ያቅስመጣቸው ቅድመ ሁኔታዎች ሳይሸራረፉ እንዲተገበሩ ለሁሉም ባለድርሻ አካላት ጥሪ አቅርቧል።