ትምህርት ሚኒስቴር በትምህርት ዘርፉ እያካሄደ ካለው የሪፎርም ስራ ውስጥ የተቀናጀ የተግባር ተኮር ጎልማሶች ትምህርት መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ ገልጸዋል፡፡
ሃገር አቀፍ የትምህርት ብርሃን የተሰኘ አዲስ የፈተና ዓይነት ይፋ ሆነ!
🔰1. ማንም ማንበብና መፃፍ የሚችል ሰው የሚፈተነው
🔰2.3ኛ ክፍል ማጠናቀቅ ጋር አቻነት ስርዓት ይዘረጋል
🔰3. በአፍ መፍቻ ቋንቋ ይሰጣል
🔰4. ያለፉት በተግባር ተኮር ትምህርት ይቀጥላሉ
➡️ ትምህርት ሚኒስቴር በትምህርት ዘርፉ እያካሄደ ካለው የሪፎርም ስራ ውስጥ የተቀናጀ የተግባር ተኮር ጎልማሶች ትምህርት መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ ገልጸዋል፡፡ በሀገራችን የመጻፍ፣ የማንበብና የማስላት ችሎታ ያላቸውን ጎልማሶች ለመለየት የሚያስችል በሀገር አቀፍ ደረጃ በተለያዩ ቋንቋዎች የተዘጋጀ የትምህርት ብርሃን ፈተና ሊሰጥ መሆኑን ሚኒስትሩ ጨምረው ተናግረዋል። በፈተናውም ውጤት ያመጡ ጎልማሶች የ3ኛ ክፍል ያጠናቀቁበት አቻ ሰርተፊኬት ይዘጋጅላቸዋል ነው ያሉት፡፡ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በትምህርት ዘርፉ እየተካሄዱ ባሉ ሪፎርሞች ላይ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጋር ምክክር እያካሄደ ነው፡፡ #MoE