ትምህርት ሚኒስቴር ለመጀመሪያ ጊዜ የ12ተኛ ክፍል ዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተናን በኦን ላይን እንደሚያከናውን መግለፁ ይታወቃል፡፡ በዚህ መሰረት ለተፈታኞቹ ታብሌት ኮምፒውተሮችን እንደሚሰጥ ታውቋል፡፡
ካፒታል የእንግሊዘኛ ጋዜጣ እንደዘገበው ፈተናው የሚሰጠው ከህዳር 28 እስከ ታህሳስ 1 ቀን 2013 አ.ም ድረስ ሲሆን የተፈታኞቹም ብዛት 450 ሺ ገደማ ነው፡፡
✅እንደ ትምህርት ሚኒስትር ውሳኔ ከሆነ ማንኛውም 11ኛ ክፍልን ያጠናቀቀና የ12ተኛ ክፍልን ያለፈውን አመት የመጀመሪያ ሴሚስተር የተማረ ተማሪ ለፈተናው መቀመጥ የሚችል ሲሆን፣ ምዝገባው የሚደረገውም በኦንላይን ነው፡፡
✅ ይሁንና ከፈተናው በፊት ተፈታኞቹ የ45 ቀናት ትምህርትና የቴክኖሎጂ መመሪያ እንዲወስዱ ይደረጋል፡፡
✅ ይህንን በተመለከተ ከካፒታል ጋዜጣ ጥያቄ የቀረበላቸው
የትምህርት ሚኒስቴር ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተሯ ወ/ሮ ሀረጓ ማሞ ለእያንዳንዱ ተፈታኝ ተማሪ ታብሌት ኮምፒውተር እንደሚሰጠው አስታውቀዋል፡፡
✅ትምህርት ሚኒስቴር በአገሪቱ ያለውን የኢንተርኔት ችግር ከግምት ውስጥ
በማስገባትም በራሱ ሳተላይት በተመረጡ ትምህርት ቤቶች ኢንተርኔት ግንኙነት ለመፍጠር መዘጋጀቱን ገልፀዋል፡፡ በተጨማሪም የስምንተኛ ክፍል ፈተና ህዳር 22 እና 23 የሚሰጥ መሆኑን የጠቆሙት ዳይሬክተሯ በአጠቃላይ በአገሪቱ በሚቀጥሉት ሶስት ሳምንታት ጊዜ ትምህርት ቤቶች በሙሉ እንደሚከፈቱ አስረድተዋል፡፡ ትምህርት ቤቶች ሲከፈቱ የተማሪዎችን አካላዊ ርቀት ለመጠበቅ በአንድ ክፍል ውስጥ ከ25 ተማሪ በላይ ማስተማር እንደማይቻልም ጨምረው
አስታውቀዋል።