የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለሚወስዱ ተማሪዎች ተቋርጦ የነበረውን ትምህርት ለመከለስ የሚያስችል የቴሌቪዥን
ፕሮግራም በትምህርት ሚኒስቴር የቴሌቪዥን ጣቢያ እንደሚሰራጭ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ፕሮግራሙ ሰባት የትምህርት ዓይነቶችን ማለትም እንግሊዘኛ፣ ሒሳብ፣ ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስ፣ ባዮሎጂ፣ ጂኦግራፊና ኢኮኖሚክስን እንደሚያካትት ተገልጿል፡፡
ፕሮግራሙ ከሰኞ እስከ እሁድ በድግግሞሽ እንደሚተላለፍ የገለፀው ሚኒስቴሩ ወላጆች ለልጆቻቸው አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ አሳስቧል፡፡
የስርጭት የጊዜ ሰሌዳውን ጨምሮ የተዘጋጀውን ፕሮግራም በአማራጭነት በሚከተሉት ማህበራዊ ሚዲያ ማግኘት እንደሚቻልም ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡
Portal - www.eict.edu.et
YouTube -Educational Plasma Programs Grade 11-12
Telegram - የኢትዮጵያ ትምህርት ቴሌቪዥን (MOE-TV)